"ዴረክ ሄዳሻህ (አዲስ መንገድ)" ፕሮጀክት

​የዴሪክ ሄዳሻህ ፕሮግራም በመንግስት ውሳኔ (የውሳኔ ቁጥር 2253 ከዴሴምቤር 21፣ 2016) ላይ የተመሰረተ እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እስራኤላውያንን ከእስራኤል ማህበረሰብ ጋር በተሻለ መልኩ ለማዋሃድ ትልቅ ሚና ከሚጫወቱት መሳሪያዎች አንዱ አበረታች እና ከተማን ዕድሳት ሂደቶችን የሚያስተዋውቅ እንደሆነ ተወስኗል (በታማ 38፣ ፒኑይ ብኑይ እና ተመሳሳይ ውጥኖች)።

በመንግስት ውሳኔ መሰረት የዴሪክ ሄዳሻህ ፕሮጀክት በውስጣቸው ከፍተኛ ብዛት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተወላጆች ባሉባቸው – አምስት መንድሮች (በተለያዩ ከተሞች) ላይ ያተኮረ ሲሆን ከእነዚህ መንደሮች ውስጥ ሦስቱ በኔታንያ ይገኛሉ፦ ኬርያት ኖርዳው፣ ራማት ያዲን (ዶራ)፣ እና ኒኦት ሼክድ (አዞሪም)። በእነዚህ መነድሮች ውስጥ ከአካባቢ እይታ ጋር ለከተማ ዕድሳት የንድፍ ዝርዝር እቅድ ማውጣት ተጀምሯል።

​​​​​​

Relevant News